Fana: At a Speed of Life!

የባቡር ትራንስፖርት ቀጠናዊ የኢኮኖሚ ትስስርን ያጎለብታል-  አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ

 

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 9፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮ-ሱዳን የባቡር ኘሮጀክት የጋራ ቴክኒክ ቡድን ስብሰባ በካርቱም መካሄድ ጀመረ።

በኢትዮ- ሱዳን ስታንዳርድ ጌጅ ባቡር መስመር ግንባታ ፕሮጀክት የአዋጭነት ጥናት ላይ የሚመክረው የጋራ የቴክኒክ ቡድን ስብሰባ በሱዳን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ባለሙሉሥልጣን አምባሳደር ይበልጣል አዕምሮ እና የሱዳን የትራንስፖርት ምክትል ሚኒስትር መሃመድ ባሸር በተገኙበት በካርቱም የተጀመረው።

አምባሳደር ይበለጣል በስብሰባው ፥ ኢትዮጵያና ሱዳን ለረጀም ዘመናት የዘለቀ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት እንዲሁም ጠንካራ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ትስስር ያላቸው አገራት መሆናቸውን ጠቅሰው፣ የባቡር ትራንስፖርት ከሁለቱ አገራት በተጨማሪ ቀጠናዊ የኢኮኖሚ ትስስርን ይበልጥ ለማጎልበት ወሳኝ ሚናን የሚጫወት መሠረተ ልማት መሆኑን ገልጸዋል።

ምክትል ሚንስትር መሃመድ በሽር በበኩላቸው የባቡር ትራንስፖርት ከባድ ጭነት በቀላል ወጭ የሚያጓጉዝ የትራንስፖርት ስርዓት እንደመሆኑ ለሁለቱ ህዝቦች ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት ጠቃሚ አለው ማለታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.