Fana: At a Speed of Life!

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ኮሚቴ ተቋቋመ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በምርጫው ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ኮሚቴ ተቋቋመ።
መጪው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ፣ዴሞክራሲያዊ እና ግልጸኝነት የሰፈነበት ሆኖ እንዲጠናቀቅ ብልፅግና ፓርቲን ጨምሮ ሌሎች ተፎካካሪ ፓርቲዎች ችግሮችን የሚፈቱበት የጋራ ኮሚቴ በከተማ ደረጃ በትናንትናው ዕለት ተቋቁሟል ።
የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አለማየሁ እጅጉ በጋራ ኮሚቴ ምስረታው ላይ እንደገለጹት ÷ምርጫው ለኢትዮጵያ ምሳሌ የሚሆንና ለህዝቡ ተስፋ የሚሰንቅ እንዲሆን ብልፅግና ቁርጠኛ አቋም ይዞ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አስረድተዋል።
ተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች በበኩላቸው የሃገር ሰላምና የከተማዋ ሰላም ሁሉንም የሚመለከት በመሆኑ በፀጥታ ጉዳዮችና በምርጫው ሂደት ላይ የድርሻቸውን እንደሚወጡ ማረጋገጣቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ኮሚቴ ፓርቲዎቹ በቀጣይ ቋሚ ግንኙነት የሚያመቻቹ አባላት ከተለያዩ ፓርቲዎች መርጠዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.