Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ለአሶሼትድ ኘሬስ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ ሰጠ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ለአሶሼትድ ፕሬስ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ መስጠቱ ተገለጸ፡፡

በቅርቡ አሶሼትድ ፕሬስ 6ተኛው ጠቅላላ ሀገራዊ ምርጫ ከመራዘሙ ጋር በተያያዘ የሰራው ዘገባ ከእውነት የራቀ መሆኑን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን አስታውቋል።

ጉዳዩን በተመለከተ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን መግለጫ ሰጥቷል።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬተር አቶ መሀመድ እድሪስ፥ ምርጫው በግልጽ እና በአደባባይ ከሎጂስቲክስ አቅርቦት እና ከአጠቃላይ ስራ መጓተት ጋር ተያይዞ ለተወሰኑ ሳምንታት መራዘሙ እየታወቀ ምርጫው የተራዘመው በትግራይ ክልል ካለው ጦርነት ጋር በተገናኘ ነው ብሎ ከእውነት የራቀ ዘገባ ሰርቷል ብለዋል።

አሶሼትድ ፕሬስ የሰራውን የተዛባ ዘገባ ተከትሎ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ መስጠቱን ዋና ዳይሬክተሩ መናገራቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።

በቀጣይም በኢትዮጵያ ፈቃድ አግኝተው በሚንቀሳቀሱ ነገር ግን ሕግ እና ስርዓትን ተከትለው በማይሰሩ መገናኛ ብዙሃን ላይ መሰል እርምጃ እንደሚወሰድ አቶ መሀመድ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.