Fana: At a Speed of Life!

ጆ ባይደን በእስራኤልና ፍልስጤም የተኩስ አቁም እንዲደረስ ጥሪ አቀረቡ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በእስራኤልና ፍልስጤም የተኩስ አቁም እንዲደረስ ጥሪ አቀረቡ፡፡

ፕሬዚዳንቱ ለእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ አሜሪካ የተኩስ አቁም እንዲደረስ ግብጽን ጨምሮ ከተለያዩ ሃገራት ጋር መስራቷን ገልጸውላቸዋል፡፡

እስራኤል የንጹሃንን ደህንነት ከግምት ውስጥ ማስገባት አለባት ያሉት ፕሬዚዳንቱ፥ አሜሪካም ይህን ታበረታታለችም ነው ያሉት፡፡

ይሁን እንጅ ባይደን በፀጥታው ምክር ቤት የቀረበውን እና እስራኤል የምትወስደውን ወታደራዊ እርምጃ እንድታቆም የሚጠይቀውን ሃሳብ ውድቅ አድርገዋል፡፡

ከዛ ይልቅ ነገሮችን በዲፕሎማሲያዊ መንገድ መፍታት ይሻላል የሚል አቋማቸውን ገልጸዋል፡፡

ፍልስጤማውያን የእስራኤል ወታደሮች በአል አቅሳ መስጊድ ወስደውታል ያሉትን እርምጃ ተከትሎ የተጀመረው ግጭት ለበርካቶች ህልፈት ምክንያት ሆኗል፡፡

እስካሁን እስራኤል በጋዛ በወሰደችው እርምጃ 212 ሰዎች ለህልፈት ሲዳረጉ በእስራኤል በኩል ደግሞ 10 ሰዎች ለህልፈት መዳረጋቸውን ዘገባዎች ያመላክታሉ፡፡

ምንጭ ፦ ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.