Fana: At a Speed of Life!

ግብፅ የጋዛ ሰርጥን መልሶ ለመገንባት 500 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ይፋ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ግብፅ በፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሀማስ እና እስራኤል መካከል እየተካሄደ በሚገኘው ግጭት ጉዳት የደረሰበትን የጋዛ ሰርጥ መልሶ ለመገንባት 500 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ይፋ አደረገች።

የግብፁ ፕሬዚዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ድጋፉ ሰሞኑን እየተካሄ በሚገኘው ግጭት ጉዳት የደረሰበትን የጋዛ ሰርጥ መልሶ ለመገንባት እንደሚውል አስታውቀዋል።

በዚህ ድጋፍ በሚካሄደው የመልሶ ግንባታ ግብፃውያን ኩባንያ እንደሚሳተፉ የፕሬዚዳንቱ ቃል አቀባይ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

ምንም እንኳን ግብፅ ይህን ድጋፍ ይፋ ያደረገች ቢሆንም በአካባቢው ያለው ግጭት አሁንም እንደቀጠለ ነው።

እስከአሁን በነበረው ግጭት በፍልስጤም በኩል 61 ህፃናት እና 36 ሴቶችን ጨምሮ 212 ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ተነግሯል።

በተመሳሳይ በእስራኤል በኩል የ10 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን በሁለቱም በኩል በርካቶች የመቁሰል አደጋ እንዳጋጠማቸው ቢቢሲ በዘገባው ላይ አስፍሯል።

የአለም ሀያላን ሀገራት የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲካሄድ ጥሪ እያቀረቡ የሚገኙ ቢሆንም እስራኤል በጋዛ ሰርጥ የምትወስደው የአየር ጥቃት እና ሀማስ ወደ እስራኤል የሚተኩሰው ሮኬት እንደቀጠለ ነው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.