Fana: At a Speed of Life!

ከ19ሺህ በላይ አረጋዊያን የሴፍቲኔት ተጠቃሚ መደረጋቸው ተነገረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ በአስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ከ19ሺህ በላይ አረጋዊያን በየወሩ የሴፍቲኔት ቀጥታ ድጋፍ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረጉን የከተማ አስተዳደሩ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ገለጸ፡፡
ቢሮው “ወቅታዊና ተግባራዊ ምላሽ ለአረጋውያን” በሚል መሪ ቃል በዓለም 30ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ29ኛ ጊዜ የአረጋውያን ቀን አክብሯል፡፡
የተለያዩ የህይወት ምዕራፍ አልፋችሁ ለዚህ እድሜ የበቁ አረጋውያንን የኢትዮጵያ ባለውለታዎች ናችሁ ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ዣንጥራር አባይ ናቸው፡፡
ኢትዮጵያን በልማቱ ዘርፍ፣ በውትድርና፣ እንዲሁም በተለያዩ የሙያ መስኮች ተሰማርታችሁ ለዚህ ስላበቃችሁ እናመሰግናለን ብለዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት መንግስት ለአረጋውያን የሚያደርገው እንክብካቤና ድጋፍ መሻሻል ማሳየቱን የገለፁት አቶ ዣንጥራር፤ አረጋውያንን ከመደገፍ ባሻገር በልማቱ ዘርፍ እንዲሰማሩ የእውቀት ፣የታሪክ፣የጥበብ ሽግግር እንዲያደርጉ ቢሮው ሰፊ ስራ መስራት ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡
የአዲስ አበባ ሰራተኛና ማህራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተፈራ ሞላ በበኩላቸው፤ ቢሯችን በአዋጅ ከተሰጠው ኃላፊነት አንፃር በአስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ ከሚገኙ 49 ሺህ 780 አረጋውያን ውሰጥ 19ሺህ 241 የሴፍቲኔት ቀጥታ ድጋፍ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸው፣ ከዚህ ባለፈም የጤና መድን አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተሰራ ማለታቸውን ከከተማ አስተዳደሩ ሰራተኛና ማህራዊ ጉዳይ ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.