Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ለከብሯ እና ነፃነቷ የማትደራደር መሆኗን ሁሉም ሊገነዘብ ይገባል-ጠ/ ሚ ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ ፣ግንቦት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ለከብሯ እና ነፃነቷ ፍፁም የማትደራደር ሀገር መሆኗን ሁሉም ሊገነበዘው እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ።

ከዛሬ ጀምሮ እስከ ግንቦት16 ቀን 2013 ዓ.ም በወዳጅነት ፓርክ የሚከበረውን የኢትዮጵያ ሳምንት መርሐ-ግብር ጠቅላይ ሚኒስትሩ በይፋ አስጀምረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ መርሐ-ግብር ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ኢትዮጵያ ለከብሯ እና ነፃነቷ ፍፁም የማትደራደር ታላቅ ሀገር መሆኗን ሁሉም ሊገነበዘው ይገባል ብለዋል።

ኢትዮጵያ በብዝኃ ማንነቶች ውስጥ ደምቃ የምትታይ፣ የጥቁር ሕዝቦች ኩራት እና የነፃነት ተምሳሌት መሆኗንም አንስተዋል።

ከፍ ብለው የሚታዩ የበርካታ ታሪኮች ባለቤት እና ልዩ የተፈጥሮ ፀጋ የተላበሰች በብዙ ማንነቶች የተገመደች ታሪካዊ ሀገር ናት ሲሉ  መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በመሆኑም የእነዚህ ሁሉ መገለጫዎች እና ታሪኮች ባለቤት የሆነችውን ሀገር ሁሉም በቅጡ ሊያውቃት እና ሊረዳት ይገባልም ነው ያሉት  ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ።

“የኢትዮጵያን እምቅ ሀብት በጋራ በማልማትና በማሳደግ ሁላችንም ለጋራ ብልጽግና መሥራት ይገባናል” ብለዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.