Fana: At a Speed of Life!

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በማንዱራ ወረዳ ያስገነቡትን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስመረቁ 

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጽሕፈት ቤት በመተከል ዞን ያስገነባውን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስመረቀ፡፡

ትምህርት ቤቱ በማንዱራ ወረዳ ወላምባ ቀበሌ የተገነባ ነው።

የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት በመጀመሪያ ዙር በሁሉም ክልሎች ካስገነባቸዉ 20 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል የሆነው ዋላምባ ብርሃን 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታውን ለመጨረስ 13 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ወጪ ተደርጎበታል፡፡

ትምህርት ቤቱ በሁለት ፈረቃ 1 ሺህ 800 ተማሪዎችን የማስተማር አቅም ያለው ሲሆን በውስጡ የቤተ ሙከራ፣ መማሪያ ክፍሎች፣ ቤተ መፅሀፍትና የኮምፒዩተር ቤተ ሙከራን ያካተተ ነው፡፡

የቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት በሁሉም ክልሎች የተሰሩትን ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች መምህራንና የአካባቢው ማህበረሰብ ጥበቃ እና እንክብካቤ እንዲያደርግ እንዲሁም ለተገነባበት አላማ ብቻ እንዲያውሉ ጥሪ አቅርቧል።

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቱ የመማሪያ ደብተር ፣ ኮሙፒውተሮች፣ሶላር መብራት ፣ቴርሞ ሜትር ፣ ጫማ እና ደብተር ድጋፍ አድርገዋል።

በምርቃት ስነ ስርአቱ ላይ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሃሰንን ጨምሮ የክልሉና የመተከል ዞን ኮማንድ ፖስት ሃላፊዎች ተገተኝተዋል፡፡

በፍሬህይወት ሰፊው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.