Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ በትራፊክ አደጋ 46 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ዛሬ ጠዋት 1:30 ላይ 61 ሰዎችን ጭኖ ወደ ባህር ዳር ይጓዝ የነበረ ታታ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ከቅጥቅጥ አይሱዙ ጋር በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ተጋጭቶ በደረሰ የትራፊክ አደጋ 46 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

በአዲስ አበበ ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ማርቆስ ታደሰ እንደገለጹት፥ በትራፊክ አደጋው ሁለቱም ተሽከርካሪዎች ተገልብጠው 46 ሰዎች ላይ ጉዳት ከመድረሱ በስተቀር እስካሁን ምንም የሞተ ሰው የለም፡፡

በትራፊክ አደጋው የተጎዱ ሰዎች ወደ አቤት ሆስፒታልና ሌሎች የህክምና ማዕከላት መወሰዳቸውንም ነው ዋና ኢንስፔክተር ማርቆስ የተናገሩት፡፡

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ ነው ያሉት ዋና ኢንስፔክተሩ የተገለበጡ ተሽከርካሪዎች በክሬን ተነስተው መንገዱ ለትራፊክ ክፍት መደረጉንም ጠቁመዋል፡፡

በሁሉም ቦታዎች እየደረሱ ያሉት የትራፊክ አደጋዎች መንስኤ ደንብ መተላለፍ መሆኑን የገለፁት ኃላፊው በተለይም ለማሽከርከር አስቸጋሪ በሆኑ መንገዶች አካባቢ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል ብለዋል፡፡

የሱሉልታ መንገድ ዳገታማ፣ ጠመዝማዛና ቁልቁለታማ በመሆኑ አሸከርካሪዎች ይህን ተረድተው ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል፡፡

ስፍራው ከዚህ በፊትም በተለያዩ ጊዜያት በርካታ አደጋዎች ሲያስተናግድ የነበረ አካባቢ እንደነበር ጠቁመው፥ በማንኛውም ቦታዎች አሽከርካሪዎች ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው መናገራቸውን የኢቢሲ ዘገባ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.