Fana: At a Speed of Life!

በዓለም አቀፍ ደረጃ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ያስከተለውን የኢኮኖሚ ጫና ለመቋቋም የሚደግፍ የ650 ቢሊየን ዶላር እንዲመደብ ተወሰነ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም አቀፍ ደረጃ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ያስከተለውን የኢኮኖሚ ጫና ለመቋቋም የሚደግፍ የ650 ቢሊየን ዶላር እንዲመደብ ተወሰነ።

በፕሬዚንዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የተመራውና የገንዘብ ሚኒስትሩን ጨምሮ ሌሎች ኃላፊዎችን ያካተተው የኢትዮጵያ ልኡካን ቡድን በፈረንሳይ ፓሪስ ከተማ በመገኘት የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ባዘጋጁት የአፍሪካ አገራት በኮሮኖ ቫይረስ ላደረሰባቸው ጉዳት የፋይናንስ ደጋፍ ለማሰባሰብ በተዘጋጀው ጉባኤ ላይ ተሳትፏል።

የገንዘብ ሚኒስቴርም ተሳትፎውን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ የኢኮኖሚ ጫናውን ለመቋቋም ከተመደበው የ650 ቢሊየን ዶላር ውስጥ 330 ቢሊየን ዶላሩ የአፍሪካ ሀገራት ድርሻ እንደሚሆን መወሰኑን አስታውቋል።

በቀጣይም በመጀመሪያ ዙር የሚፈለገውን ገንዘብ ለማስገኘት እንደሚሰራ ተጠቁሟል፡፡

በቅርቡ የአለም የገንዘብ ድርጅት ባወጣው ሪፓርት ታዳጊ የአፍሪካ ሀገራት የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ካደረሰባቸው የኢኮኖሚ ጉዳት ለመቋቋም እና ለማገገም እንዲችሉ እስከ ፈረንጆቹ 2025 ድረስ እስከ 330 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር እንደሚያስፈልግ ተገልጿል።

የአፍሪካ ሀገራት የፋይናንስ ጉባኤ ዋና አላማውም ወረርሽኙ ካስከተለው ተጋላጭነት፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ጫና የአፍሪካ አገራት መውጣት እንዲችሉና በኢኮኖሚ እድገታቸውም የተሻለ አፈጻጸም እንዲያስመዘግቡ፣ ብሎም እንደ ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ ሪፎርም ትግበራ ላይ ያሉ ሀገራትም ዕቅዳቸውን በተሳካ ሁኔታ ተግባራዊ እንዲያደርጉና ጠንካራ መሰረት ያለው ኢኮኖሚ እንዲኖራቸው ለማስቻል የሚያስፈልገውን ከፍተኛ ፋይናንስ ከበለፀጉ የአለም አገራትና ከአለም አቀፍ የፋይናንስ ድርጅቶች በማሰባሰብ በተለያዩ የፋይናንስ አማራጮች ድጋፍ ለመስጠት ነው ተብሏል፡፡

በጉባኤው ላይ የተገኙት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በወረርሽኙ ምክንያት የኢኮኖሚ ድቀት ለደረሰባቸው ታዳጊ የአፍሪካ ሀገራትን በፋይናንስ ለመደገፍ የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የቀረበውን ጥሪ፣ ከአለም ሀገራትና ከአለም አቀፍ የፋይናንስ ድርጅቶች የተሰተጠውን አዎንታዊ ምላሽ በማመስገን የተከሰተው ቀውስና ከፍተኛ ችግር የሚመጥን አፋጣኝ ምላሽ ለአፍሪካ ሀገራት መስጠት አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም የአፍሪካ ሀገራት ያለባቸውን ከፍተኛ የዕዳ ጫና በተለይም ወረርሽኙ ካስከተለው ቀውስ ጋር ተደምሮ ጫናው እየተባባሰ መሆኑን በመጠቆም በፓሪስ ክለብ በኩል የተጀመረው የዕዳ ሽግሽግ ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አበዳሪ ሀገራትም ለአፍሪካ ሀገራት የሚያደርገትን ድጋፍ በሚፈለገው መጠን እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡

በሌላ መልኩም የኮሮና ቫይረስ ክትባት ለታዳጊ ሀገራት ለማዳራስ ተግባራዊ የሆኑት ኢኒሼቲቮችን በማመስገን ነገር ግን ያለው የአቅርቦት አፈፃፀም መዘግየት ላይ አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰው መጠየቃቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ጉባኤው ሲጠናቀቅም የክትባት አቅርቦት አስመልክቶ ከፍተኛ ስራ የሚያስፈልገው መሆንና ክትባቱ በተመረጡ የአፍሪካ ሀገራት የሚመረተትበትን ሁኔታ በመደገፍ የተሻለ ተደራሽነትን ለማረገጋረጥ ስራ መጀመሩ ተጠቅሷል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.