Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ከ960 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት ክፍት ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በአራት ክፍለ ከተሞች ከ960 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው ከ427 በላይ ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደረጉ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ በሳምንቱ መጨረሻ በክፍለ ከተሞች እና በወረዳ ደረጃ በህብረተሰቡ ተሳትፎ እና በመንግስት በጀት ነው ፕሮጀክቶቹ ለአገልግሎት ክፍት የተደረጉት፡፡

በጉለሌ ክፍለ ከተማ ከ151 በላይ የተለያዩ ፕሮጀክቶች፣ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ከ152 በላይ ፕሮጀክቶች እና በአራዳ ክፍለ ከተማ ደግሞ ከ47 በላይ ፕሮጀክቶች እንዲሁም ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ከ77 በላይ ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል፡፡

በሶስቱ ክፍለ ከተሞች ብቻ በጠቅላላው ከ960 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው ሲሆን፥ ፕሮጀክቶቹ የነዋሪዎችን የልማትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ደረጃ በደረጃ የህዝብን ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችሉ ናቸው ተብሏል፡፡

ለአገልግሎት ክፍት ከተደረጉ ፕሮጀክቶች መካከል በትምህርት ዘርፍ ፣በጤናው ፣በስራ እድል ፈጠራ፣ በወጣቶች ስብዕና መገንቢያና ስፖርት ማዘውተሪያ እንዲሁም የቢሮ ግንባታና ማስፋፊያ ስራዎች ይገኙበታል፡፡

በቀጣይ ሳምንትም በቀሪዎቹ ክፍለ ከተሞች በርካታ ፕሮጀክቶችን ለአገልግሎት ክፍት ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ ከአዲስ አበባ ፕረስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.