Fana: At a Speed of Life!

ሁለተኛው ዙር የህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት የግብፅ ፍላጎት ላይ ተፅዕኖ አይኖረውም- የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሁለተኛው ዙር የህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት የግብፅ ፍላጎት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ አንደማይኖረው የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜህ ሹክሪ ገለፁ።

ግብፅ በአስዋን ግድብ ያላት የውሃ ክምችት መተማመን እንደፈጠራላት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ “ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት የግብፅ ፍላጎት ላይ ተፅዕኖ እንደማይኖረው እንተማመናለን” ሲሉ ነው የገለፁት።

ግብፅ ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ዙር የውሃ ሙሌት ከማከናወኗ በፊት ጀምሮ ሙሌቱ የውሃ እጥረት እንዲከሰት ያደርጋል በሚል ሂደቱን ስትቃወም ቆይታለች።

አሁንም ኢትዮጵያ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት ከማከናወኗ በፊት በተለያዩ መንገዶች እና ውይይቶች ተመሳሳይ ቅሬታ ስታቀርብ መቆየቷ የሚታወስ ነው።

ግብፅ ኢንዲፔንዳንት እንደዘገባው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከአንድ የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር በነበራቸው ቆይታ በአፍሪካ ህብረት ከሚመራው የሶስትዮሽ ውይይት እና ከአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች አንስተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.