Fana: At a Speed of Life!

ዳሸን ቢራ ፋብሪካ ከ15 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ለሚያስገነባው ትምህርት ቤት የመሰረት ድንጋይ አስቀመጠ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ዳሸን ቢራ ፋብሪካ ከ15 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ በደብረ ብርሀን ከተማ ትምህርት ቤት ሊያገነባ ነው፡፡

ፋብሪካው የሚያስገነባው አጼ ዘርያዕቆብ ሁለተኛ ደረጃ  ትምህርት ቤት የሚል መጠሪያ ያለው  መሆኑ ተመላክቷል።

አጼ ዘርያዕቆብ ትምህርት ቤት ከዚህ በፊት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ሲሆን ይህ ግንባታ ሲጠናቀቅ ትምህርት ቤቱ ደረጃውን ያሻሽላል ተብሏል።

ትምህርት ቤቱን ከዳሸን ቢራ ፋብሪካ በተጨማሪ የአማራ ልማት ማህበር (አልማ) ድጋፍ ያደርግለታል ተብሏል።

በዛሬው ዕለትም የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት በተገኙበት የትምህርት ቤቱ የመሰረት ድንጋይ ተጥሏል፡፡

በአላዩ ገረመው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.