Fana: At a Speed of Life!

በአጣዬና አካባቢው ለደረሰው ጉዳት መልሶ ማቋቋሚያ ከ30 ሚሊየን ብር በላይ ደጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ሸዋ ዞን በአጣዬና አካባቢው ለደረሰው ጉዳት መልሶ ማቋቋሚያ የሚሆን ከ30 ሚሊየን ብር በላይ ደጋፍ ተደረገ፡፡

ድጋፉ በአማራ ልማት ማህበር አስተባባሪነት በኬኬ አክሲዮን ማህበር፣ ሴንቸሪ ሞል፣ አቶ በላይነህ ክንዴ እና አዲስ አበባ ስራ አመራር ኢንስቲቲዩት የተደረገ ነው፡፡

ኬኬ የ20 ሚሊየን ብር 60 ሺህ ቆርቆሮና ብርድ ልብስ፣ አቶ በላይነህ ክንዴ የ1 ሚሊየን ብር 13 ሺህ ሊትር ዘይት ድጋፍ ሲያደርጉ ቀሪውን ሌሎች ድርጅቶችና ባለሃብቶች ሰጥተዋል፡፡

ዛሬ የተደረገው ድጋፍ የወደሙ 1 ሺህ 500 መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት የሚያስችል ከ60 ሺህ በላይ የቤት ክዳን ቆርቆሮና ሚስማር ነው፡፡

የአልማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መላኩ ፈንታ በርክክቡ ወቅት እንዳሉት አጣዬና አካባቢውን መልሶ ለመገንባት የባለሀብቶች ርብርብ የሚደነቅ ነው፡፡

በአጣዬ ከተማ መጠለያ ውስጥ ያሉ ዜጎችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ 70 ሚሊየን የሚጠጋ ባህር ዛፍ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን፥ በቅርብ ቀናት ውስጥ መኖሪያ ቤቶችን በመገንባት ነዋሪዎችን ወደ ቀያቸው እንመልሳለን ብለዋል፡፡

ድጋፍ ያደረጉ ባለሀብቶች ይህ ድጋፍ ቀጣይነት እንዳለው ገልጸዋል፡፡

አጣዬ ከተማ በአሁኑ ሰዓት መረጋጋት ውስጥ ያለች ሲሆን ነዋሪዎቿም ወደ ከተማዋ እየገቡ ነው፡፡

በአላዩ ገረመው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.