Fana: At a Speed of Life!

ዶ/ር አብርሃም በላይ የመሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ የስራ እንቅስቃሴን ጎበኙ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር አብርሃም በላይ የፋብሪካው አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታና ቀጣይ የስራ አቅጣጫ ለመስጠት በስፍራው ተገኝተው ጎብኝተዋል።
ዶክተር አብርሃም በላይ በጉብኝታቸው ወቅት ከፋብሪካው የስራ ሃላፊዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።
በውይይታቸውም የመሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ከመስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጅነሪንግ ጋር በመተባበር እየሰራ ያለውን የጥገና ስራና የምርት ሁኔታ በተሻለ ፍጥነት የሚፈጽምበትን ሁኔታ በተመለከተ አቅጣጫ ተቀምጧል::
ከዚህ በተጨማሪም የሲሚንቶ ተደራሽነት በትግራይ ህዝብ ፍላጎትና ልማት ቅድሚያ ተሰጥቶ እንዲሰራ የተጠቆመ ሲሆን ፍትሃዊ የሆነ ተደራሽነት እንዲኖርና አዳዲስ የስራ ዕድል መፍጠር ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራ የሚያስችል ማስተካከያ እንደሚደረግም ተገልጿል::
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር አብርሃም በላይ በመቐለና አካባቢው ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በጊዜያዊ መጠለያ የሚገኙ ዜጎች ያሉበትን ሁኔታም ተመልክተዋል።
ከመጠለያዎቹ ተወካዮችና አስተባባሪዎች ጋር በተደረገ ምክክርም በሰብአዊ ድጋፎች ረገድ ያጋጠሙ ችግሮች ታርመው ፍትሃዊ ተደራሽነትን አስተማማኝ በማድረግ ድጋፉን ለማስቀጠል የሚያስችል አቅጣጫ መቀመጡን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.