Fana: At a Speed of Life!

የምርጫ ካርድ የወሰዱ ዜጎች በዕለቱ ድምጽ ለመስጠት አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ እንዳለባቸው ምሁራን ተናገሩ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ለመሳተፍ የምርጫ ካርድ የወሰዱ ዜጎች በምርጫው ዕለት ድምጽ ለመስጠት አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ እንዳለባቸው ምሁራን ተናግረዋል፡፡
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት ምሁራን እንደገለጹት÷ ዜጎች የምርጫ ካርድ ከመውሰድ ባሻገር ተፎካካሪ ፓርቲዎች የሚያቀርቧቸውን ፖሊሲዎች በንቃት መከታተል እና መወሰን ይጠበቅባቸዋል፡፡
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ መምህር ዶክተር ባምላክ ይደግ ጠንካራዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንባት ዜጎች ምክንያታዊ እና በእውቀት ላይ የተመሰረተ ምርጫ ማካሄድ አለባቸው ብለዋል፡፡
ለዚህም በምርጫው ለመሳተፍ ካርድ የወሰዱ ዜጎች ተፎካካሪ ፓርቲዎች የሚያነሷቸውን አማራጭ የፖሊሲ ሃሳቦች በትኩረት መከታተል ይጠቅባቸዋል ነው የሚሉት፡፡
በሌላ በኩል ምርጫው ሰላማዊ በሆነ መልኩ እንዲከናወን በምርጫው ዕለት በመራጮች ላይ ተጽእኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ ውጫዊ ሃይሎችን ማስወገድ እንደሚገባ ነው ዶክተር ባምላኩ የሚናገሩት፡፡
በዲላ ዩኒቨርሲቲ የህግ መምህር የሆኑት አቶ አማኑኤል ታደሰ በበኩላቸው ምርጫ ካርድ የወሰዱ ዜጎች ምርጫው ሊካሄድ የቀሩትን ቀናት ግምት ውስጥ በማስገባት አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ማካሄድ እንዳለባቸው ነው የሚገልጹት፡፡
በዚህ መሰረት ፓርቲዎች በተለያዩ አማራጮች የሚያስተዋውቋቸውን ፖሊሲዎች በጥሞና መከታተል እና መመርመር እንዳለባቸው ይናገራሉ፡፡
ይህም በቀጣይ የሚያስተዳድራቸውን ፓርቲ በመለየት ውሳኔ ላይ እንዲደርሱ ያስችላቸዋል ነው የሚሉት፡፡
በመላኩ ገድፍ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.