Fana: At a Speed of Life!

የህዳሴው ግድብ ሁለተኛ ዙር ሙሌት በተያዘለት ጊዜ ይካሄዳል – አቶ ደመቀ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 13፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በተያዘለት ጊዜ እንደሚካሄድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ተናገሩ።

በጎረቤት ሃገራትና ታላላቅ ሃይቆች ክልል የሚገኙ የኢፌዴረ ሚሲዮኖች ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋና መስሪያ ቤትጋር በመተባበር “የናይል ፍትሃዊ አጠቃቀም፣ የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ለክልላዊ ትብብር ያለው ሚና” በሚል ርዕስ በተዘጋጀው የበይነ መረብ ውይይት ላይ ተሳትፈዋል።

የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በሶስቱ ሃገራት የተመራማሪዎች ብሄራዊ ቡድን በወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እንደሚካሄድ አቶ ደመቀ መኮንን ገልፀዋል።

የሶስትዮሽ ድርድሩ ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ መርህ መሰረት ውጤታማ እንዲሆን የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ያላቸውን እምነት አረጋግጠዋል።

ግብፅና ሱዳን ጉዳዩን ዓለም አቀፋዊ በማድረግ በኢትዮጵያ ላይ ጫና እንዲደረግ ጥረት እያደረጉ ስለመሆኑም አውስተዋል።

በስብሰባው ተሳታፊ የነበሩት የደቡብ ሱዳን ምክትል የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ጉዳዮች ሚኒስትር ደንግ ዳው ደንግ በበኩላቸው ታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ የሰላም ፕሮጀክት መሆኑን አውስተዋል፡፡

የሀገራቸው ፓርላማ በቅርቡ የናይል ስምምነት ማዕቀፍን እንደሚያፀድቅ አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ የሶሰትዮሽ ድርድር ሁሉን ተጠቃሚ የሚያደርግ ስምምነት ላይ በመድረስ እልባት እንደሚያገኝ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል።

በወቅቱም የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር የቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኢንጂነር ጌዲዮን አስፋውና ሌሌች የዘርፉ ባለሙያዎች የውይይት መነሻ ፅሑፍ ማቅረባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.