Fana: At a Speed of Life!

እስራኤል እና ፍልስጤም በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 13፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) እስራኤል እና የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሐማስ በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት ተግባራዊ ማድረግ ጀመሩ፡፡

የተኩስ አቁም ስምምነቱ ለ11 ቀናት የሚቆይ ሲሆን፥ ባለፉት ቀናት በነበረው የተኩስ ልውውጥ ከ240 በላይ ሰዎች ለህልፈት ተዳርገዋል፡፡

ፍልስጤማውያን ዛሬ የተጀመረውን የተኩስ አቁም ተከትሎ ወደ ጎዳናዎች ወጥተዋል፡፡

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የተኩስ አቁም ስምምነቱ  እውነተኛ ዕድል ይዞ የመጣ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

እስራኤል ሐሙስ ዕለት በሰሜናዊ ጋዛ በሐማስ መሠረተ ልማት ላይ ያነጣጠረ ከ100 በላይ የአየር ድብደባ  ያደረገች ሲሆን ÷ ሃማስ በበኩሉ ከ300 በላይ ሮኬቶችን ወደ እስራኤል ማስወንጨፉን የእስራኤል ጦር አስታውቋል፡፡

ፍልስጤማውያን የእስራኤል ወታደሮች በአል አቅሳ መስጊድ ገብተው ወስደውታል ያሉትን እርምጃ ተከትሎ  ግጭት መከሰቱ ይታወሳል።

በዚህም በጋዛ ከ100 በላይ ሴቶችን እና ሕፃናትን ጨምሮ ቢያንስ 232 ሰዎች ለህልፈት ሲዳረጉ፥ በጋዛ ከተገደሉት መካከል ቢያንስ 150 ታጣቂዎች መሆናቸውን እስራኤል ስትገልጽ ቆይታለች።

በእስራኤል በኩል ሁለት ህፃናትን ጨምሮ 12 ሰዎች መገደላቸውን የሃገሪቱ ጤና ሚኒስቴር ገልጿል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.