Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ህብረት በቻድ ዴሞክራሲያዊ ሽግግር እንዲደረግ ጥሪ አቀረበ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 13፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአፍሪካ ህብረት በቻድ ዴሞክራሲያዊ ሽግግር እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል፡፡
ባሳለፍነው ሚያዚያ ወር የሃገሪቱ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ኢድሪስ ዴቢ በውጊያ ወቅት በደረሰባቸው የመቁሰል አደጋ ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል፡፡
ይህን ተከትሎም ሃገሪቱ በልጃቸው በሚመራው ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት እየተዳደረች ትገኛለች፡፡
ህብረቱ ማንኛውንም የሽግግር ማራዘሚያ ጊዜ እንደማይቀበልም አስታውቋል፡፡
የቻድ ወታደራዊ ምክር ቤት በበኩሉ በ18 ወራት ውስጥ ምርጫ ለማካሄድ ቃል ገብቷል ፡፡
ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤቱ ስልጣኑን ከተረከበ ጊዜ ጀምሮ መደበኛ የተቃውሞ ሰልፎች የተካሄዱ ሲሆን በርካታ ማህበረሰብ አንቂዎችም ለእስር ተዳርገዋል ነው የተባለው፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.