Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ደቡባዊ ዞን የተማሪዎች ምዝገባ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ደቡባዊ ዞን ትምህርት ለማስጀመር የተማሪዎች ምዝገባ መጀመሩን በክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር የዞኑ ማህበራዊ ጉዳይ መመሪያ አስታወቀ።

የመምሪያው አስተባባሪ አቶ አብርሃ ደሳለው እንደገለጹት፤ የተማሪዎች ምዝገባ የተጀመረው በሁለተኛና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ነው።

ምዝገባው ከተጀመረባቸው የዞኑ አካባቢዎች መካከል መኾኒ እና አዲሸሁ ከተሞች እንደሚገኙበት ጠቅሰው፤ ምዝገባውን በማጠናቀቅ በአጭር ጊዜ ውስጥ ትምህርት እንደሚጀመር ኢዜአ ዘገቧል።

ተማሪዎች ትምህርት በሚጀምሩበት ወቅት ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ እንዳይሆኑ 40ሺህ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብል፤ እንዲሁም ሳኒታይዘር ዝግጁ ተደርጓል ብለዋል።

በማይጨውና ሌሎች የዞኑ አካባቢዎች የተማሪዎች ምዝገባ ለማስጀመር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም አቶ አብርሃ ጠቁመዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.