Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ፣ ካሪቢያን እና የፓስፊክ መንግስታት ድርጅት ለዶ/ር አርከበ እቁባይ ድጋፉን ገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 13፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአፍሪካ፣ ካሪቢያን እና የፓስፊክ መንግስታት ድርጅት የአምባሳደሮች ኮሚቴ በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ህብረት ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ዋና ዳይሬክተርነት በእጩነት ለቀረቡት ለዶክተር አርከበ እቁባይ ድጋፉን ገለፀ።

ዶክተር አርከበ እቁባይ ለአፍሪካ፣ ካሪቢያን እና የፓስፊክ መንግስታት ድርጅት የአምባሳደሮች ኮሚቴ ተመድ የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ዋና ዳይሬክተርነት ሆነው ከተመረጡ ሊሰሯቸው ስለሚችሉ ስራዎችና ስኬቶቻቸው ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በዚህ ወቅትም አረንጓዴ ተኮር የሆነው ኢንዱስትሪ መር የበለጠ ለማሳደግ እና ፆታዊ እኩልነት እና ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ እንደሚሰሩ መናገራቸውን ከድርጅቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

የአፍሪካ፣ ካሪቢያን እና የፓስፊክ መንግስታት ድርጅት የአምባሳደሮች ኮሚቴም ዶክተር አርከበ ለቦታው ብቁ እንደሆኑ እና የድርጅቱ አባል ሀገራት በምርጫ ወቅት ድምፃቸውን እንዲሰጧቸው ጥሪ አቅርቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.