Fana: At a Speed of Life!

ኤጀንሲው ከከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ለሲቲ-ኔት እና ስማርት ሰርቪስ ዴሊቨሪ ትግበራ ጥናት ለማድረግ ከከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሹመቴ ግዛው ÷ ኤጀንሲው የሳይበር ደህንነትን በሀገሪቱ ለማረጋገጥ በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

አሁን ላይ ከከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ጋር የተፈረመው የመግባቢያ ሰነድም ይህን ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል፡፡

የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሃመድ በበኩላቸው÷በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በኩል ከተሞችን ለማዘመን በርካታ ስራዎች መጀመራቸውን ገልጸዋል

እነዚህን ሲስተሞች በተጠናከረ፣ በተሳለጠ እና ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ ተግባራዊ ለማድረግ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ጋር በጋራ ለመስራት መወሰናቸውን አብራርተዋል፡፡

በመግባቢያ ስምምነቱ መሰረት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር በሀገሪቱ በሚገኙ 117 ከተሞች ላይ ሊተገበር ላሰበው ለሲቲ-ኔት እና ስማርት ሰርቪስ ተደራሽ የማድረግ እቅዱ ግብዓት የሚሆኑ ጥናቶችን በጥቂት ወራት ውስጥ አዘጋጅቶ ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እንደሚያስረክብ ከኢመደኤ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.