Fana: At a Speed of Life!

አዲሱ የቴክኒክና ሙያ ፖሊሲ  የተያዙ የልማት ዕቅዶችን የሚያሳካ ነው ተባለ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ የተዘጋጀው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲና ስትራቴጂ በየሴክተሩ የተያዙ የልማት ዕቅዶችን የሚያሳካ ነው ሲሉ የዘርፉ ባለድርሻ  እና አጋር አካላት ገለፁ፡፡

ይህ የተገለጸው ኤጀንሲው በዘርፉ ፖሊሲና ስትራቴጂው ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር ባዘጋጀው መድረክ ላይ ነው፡፡

በመድረኩ የፌዴራል ተቋማት፣ የአጋር ድርጅቶችና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ተቋማት  የተገኙ ሲሆን÷ አዲስ የተዘጋጀው የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ፖሊሲና ስትራቴጂ ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡

የሥራ ኃላፊዎቹ በውይይቱ ላይ እንደገለፁት የተዘጋጀው ፖሊሲና ስትራቴጂ ከዚህ ቀደም የሚነሱ ችግሮችን የሚቀርፍ ከመሆኑ ባለፈ በየሴክተሩ የተያዙ የልማት ዕቅዶች እንዲሳኩ የሚያግዝ ነው ፡፡

የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ክብረት በበኩላቸው÷ ፖሊሲው በትምህርትና ሥልጠና ፍኖተ ካርታ የተቀመጡ ምክረ ሀሳቦችን መሰረት ተደርጎ የተሰራ ነው ብለዋል፡፡

በዚህም እንደ ሀገር በቀጣይ ዓመታት የተያዙ ዕቅዶች እንዲሳኩ የሚያስፈልገንን የሰለጠነ የሰው ሃይል ታሳቢ ያደረገ ሲሆን÷ ለዚህም ሁሉም አካላት በባለቤትነት ይዘው ሊሰሩ ይገባል ማለታቸውን ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.