Fana: At a Speed of Life!

አቶ እርስቱ ይርዳ ከ190 ሚሊየን ብር በላይ ለሚገነባው የሳውላ የንጹህ መጠጥ ውሃ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ አኖሩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳ ከ190 ሚሊየን ብር በላይ ለሚገነባው የሳውላ የንጹህ መጠጥ ውሃ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል፡፡

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ከዚህ ቀደም የዞኑ ህዝብ ካቀረባቸው የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች ውስጥ አንዱ የንጹህ መጠጥ ውሀ እንደነበር ተናግረዋል፡፡

በዚህም መንግስት የህብረተሰቡን የመሠረተ የልማት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ቃል በገባው መሰረት የሳውላ ከተማ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት እውን ለማድረግ የመሠረት ድንጋይ የማኖር መርሀ ግብር ለዚህ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

በዞኑ የወጣቶችን የስራ ፈጠራ ተጠቃሚነት ለማጎልበት የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋም እንዲገነባ ህብረተሰቡ ያቀረበውን ጥያቄ መነሻ በማድረግ ተቋሙን መገንባት የሚያስችል ጨረታ ሂደት ላይ መሆኑንም አብራርተዋል፡፡

ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ በሳውላ ከተማ በህብረተሰቡ ተሳትፎ እና በመንግሥት ድጋፍ የሚገነባውን የከተማ የውስጥ ለውስጥ አስፋልት መንገድ ግንባታ የመሠረት ድንጋይም አኑረዋል፡፡

በፕሮግራሙ የደቡብ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ጥላሁን ከበደ፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የዴሞክራሲ ማዕከል ግንባታ ዘርፍ አስተባባሪ ሚኒስትር አቶ ተስፋዬ በልጅጌ እና ሌሎች የክልል እና የፌደራል የስራ ሀላፊዎች መገኘታቸውን ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.