Fana: At a Speed of Life!

በስልጤ ዞን ለተጎጂዎች 46 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 13፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በስልጤ ዞን በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ሀብት ንብረታቸው ለወደመባቸው ተጎጂዎች 46 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገ፡፡
የገቢዎች ሚኒስቴርና የጉምሩክ ኮሚሽን በጎርፍ፣ በእሳት ቃጠሎ እና በመሬት መንሸራተት አደጋ ምክንያት ቋሚ ንብረታቸውና የእንስሳት ሀብቶቻቸው ለወደመባቸውና ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ነው ድጋፍ ያድረገው፡፡
46 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር የሚገመት የምግብ ምርቶች እና የአልባሳት ድጋፍ በዛሬው ዕለት የጉምሩክ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ሙሉጌታ በየነ በተገኙበት ከዞኑ አስተዳደር ጋር ርክክብ መደረጉን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ተቋማቱ በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋ ዜጎች ላይ በሚደርሱ ጉዳቶች ድጋፋቸውን ሲያደርጉ መቆየታቸውን የገለፁት ምክትል ኮሚሽነሩ፥ በስልጤ ዞን በተፈጥሮ አደጋ ሀብት ንብረታቸው ለወደመባቸው ወገኖች የተደረጉት ድጋፎች የወገን ደራሽነትን የሚያረጋግጥ ተግባር ማሳያ መሆኑ በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ወቅት ተናግረዋል፡፡
የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሊ ከድር በበኩላቸው በተደረገላቸው ድጋፍ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው ድጋፉ ለወገን ደራሽ ወገን መሆኑን እና የወንድማማችነት ስሜት ታይቶበታል ነው ያሉት፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.