Fana: At a Speed of Life!

ሁለተኛው የኢትዮ-ብራዚል የጋራ ፖለቲካዊ ምክክር ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 14፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሁለተኛው የኢትዮ-ብራዚል የጋራ ፖለቲካዊ ምክክር ተካሄደ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና የብራዚል አቻቸው አምባሳደር ኬኔት ዲኖሪንጋ የተሳተፉበት ሁለተኛው የኢትዮ-ብራዚል ፖለቲካዊ ምክክር የጋራ ክልላዊና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች የጋራ ትብብሮች ላይ ያተኮረ ነበር ።

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር፣ በመጪው 6ኛው ብሔራዊ ምርጫ፣ በኢትዮ-ሱዳን የድንበር ጉዳይ እንዲሁም በትግራይ ክልል የሰብዓዊ እርዳታ ተደራሽ ለማድረግ የተከናወኑ ተግባራትን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ኢትዮጵያ ከብራዚል በተለያዩ መስኮች ለመስራት ፍላጎቷን ገልፀው ሃገራቱ በግብርና መሰረተ ልማት ዘርፎች ትብብራቸውን ማጠናከር እንደሚገባቸውም አንስተዋል።

አምባሳደር ኬኔት ዲኖሪንጋ ብራዚል ከአፍሪካ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማሳደግ ከኢትዮጵያ ጋር በቅርበት የመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡

አያይዘውም ኢትዮጵያ በአህጉሩ ያላትን ሚና በመጠቀም ግንኝነቷን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ፍላጎት እንዳላት አስረድተዋል።

ሃገራቸው ዘመናዊ ግብርና እንዲሁም በግብርና ማቀነባበር ዘርፍ በኢትዮጵያ በኢንቨስት መስኮች ለመሰማራት ዝግጁ ናት ብለዋል።

በፍትህና ፀጥታ ዘርፎች በትብብር ለመስራት እንዲሁም በባለብዙ ወገን መድረኮች ያላቸውን ትብብር ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዩች ዙሪያ ምክክር ተደርጓል።

ሁለቱ ሃገራት መካከል ለ70 ዓመት የዘለቀ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዳላቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.