Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ከ246 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ ፕሮጀክቶች ተመረቁ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቂርቆስ ክፍለ ከተማ እና በ246 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነቡ ፕሮጀክቶች ተመረቁ።

ፕሮጀክቶቹ ለ3 ሺህ 292 ሰዎች ጊዜያዊ እና ቋሚ የስራ ዕድል እንደሚፈጥሩም ተገልጿል፡፡

ከዚህ ባለፈም ለተጠቃሚዎች 279 ሚሊየን 616 ሺህ 231 ብር የገበያ ትስስር እንደሚፈጥሩም ነው የተገለጸው፡፡

ፕሮጀክቶቹ ትምህርት ቤቶች፣ መማሪያ ክፍሎች ፣ የመመገቢያ አዳራሾች፣ የተማሪዎች ምገባ እና ማብሰያ ክፍሎች፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ሜዳዎች፣ የጤና ተቋማት ማስፋፊያ እና እድሳት፣ የቂርቆስ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ማስፋፊያ ፕሮጀክቶችን ያካተቱ ናቸው፡፡

በምረቃ መርሃግብሩ ላይ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ ፥ የምርጫ ጉዳዮች አስተባባሪ ሚኒስትር አቶ ዛዲግ አብርሃ እና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።

በይስማው አደራው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.