Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ ሁለተኛው ዙር የፅዳት ዘመቻ ንቅናቄ መርሐ-ግብር ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ሁለተኛው ዙር የፅዳት ዘመቻ ንቅናቄ መርሐ-ግብር ተጀምሯል።

መርሐ-ግብሩ ለሁለት ወራት የሚቆይ ሲሆን “የከተማችን የፍሳሽ ማስተላለፊያ መስመሮች የውኃ መውረጃ እንጂ የቆሻሻ መጣያ አይደሉም” በሚል መሪ ቃል ይካሄዳል።

በዛሬው ዕለት በተለያዩ ክፍለከተሞች የተጀመረው መርሐ-ግብር መጪውን የክረምት ወራት የጎርፍ አደጋን አስቀድሞ ለመከላከል እና በቆሻሻ የተደፈኑ የፍሳሽ መውረጃ መስመሮችን ለማፅዳት ታሳቢ ያደረገ ነው ተብሏል።

የፅዳት ዘመቻው ንቅናቄ በዋናነት መንገዶች ባለሥልጣን፣ ደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ኤጀንሲ፣ ተፋሰስ እና አረንጓዴ ልማት ኤጀንሲ እና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ ተቋማት በቅንጅት የሚሠራ መሆኑ ተጠቁሟል።

የፅዳት ንቅናቄ መርሐ-ግብሩን የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በይፋ ያስጀመሩ ሲሆን የሀገር መከላከያ ሠራዊት እና የፀጥታ አካላት፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የፅዳት አምባሳደሮች፣ የፅዳት ማኅበራት ፣ የተቋማት እና የመንገድ ፅዳት ሠራተኞች በፅዳት ዘመቻው መሳተፋቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

“እኔ ለከተማዬ ውበት አምባሳደር ነኝ” በሚል መሪ ቃል ሁሉ አቀፍ የፅዳት ዘመቻ ንቅናቄ ከየካቲት እስከ ሚያዝያ ድረስ ባለፉት ሁለት ወራት መካሄዱ ይታወሳል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.