Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል ለሰብዓዊ ድጋፍ እና የተጎዱ መሠረተ ልማቶች 40 ቢሊዮን ብር ወጪ ተደርጓል- የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር

 

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግሥት በትግራይ ክልል ለሰብዓዊ ድጋፍ እና የተጎዱ መሠረተ ልማቶችን ለመገንባት እስካሁን 40 ቢሊዮን ብር ወጪ ማድረጉ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሙሉቀን ሀፍቱ ተወያይተዋል።

በውይይቱ ላይ የተሳተፉት የክልሉ ተወላጆች በትግራይ ክልል የሚደረገው አስቸኳይ የሰብዓዊ ድጋፍ የበለጠ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

በአጭር ጊዜ ውስጥ የሀገሪቱን ብሎም የክልሉን ሰላም እና መረጋጋት ለማስፈንም መንግሥት በቁርጠኝነት መሥራት እንዳለበትም አሳስበዋል።

በትግራይ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የስልክ እና መብራትን ጨምሮ ሌሎች መሠረተ ልማቶች አገልግሎት እንድጀምሩም ተወያዮቹ ጠይቀዋል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሙሉቀን ሀፍቱ፣ ክልሉን አሁን ካጋጠመው ችግር ውስጥ ለማውጣት ጊዜያዊ አስተዳደሩ ከፌዴራል መንግሥት ጋር በጋራ እየሠራ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ምንጭ፡- ኢቢሲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.