Fana: At a Speed of Life!

ሀገር በቀል እውቀቶች ማዕከላት ሊንኖራቸው ይገባል- ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሡ

 

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በወሎ ዩኒቨርሲቲ ሀገር በቀል እውቀት ላይ ያተኮረ 6ኛው አለም አቀፍ አውደ ጥናት እየተካሄደ ነው፡፡
 
አውደ ጥናቱ ወረሽኝን ለመከላከልና ለሀገር ሰላም ግንባታ በሚል መሪ ሀሣብ እየተካሄደ የሚገኘው።
 
በሀገር አቀፍ ደረጃ የተመረጡ 19 የጥናትና ምርምር ስራወች በአውደ ጥናቱ ይቀርባሉ።
 
የየሣይንስና የከፍተኛ ትምህርት ሚንስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሡ፥ የኢትዮጵያ ወቅታዊ ችግሮች መሻገሪያዎች የሀገር በቀል እውቀቶ ናቸው ብለዋል።
 
ዩኒቨርሲቲወችም የሀገር በቀል እውቀት ዕከላት እንዲኖራቸው ያስፈልጋል ይህንንም አቅደን እየሠራን ነው ያሉት ፕሮፌሰር አፈወርቅ በሀገር በቀል እውቀት የተቋማትና የምሁራን ትብብር እንዲኖር መሠራት አለበት ሲሉም አሳስበዋል።
 
የወሎ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ዶክተር አጸደ ተፈራ በበኩላከው ሀገራችን የተሠራችው በራሳችን ሁለንተናዊ ሀገር በቀል እውቀቶች በመሆኑ ከእነርሱ ስናፈነግጥ ለጥፋትና ለውድቀት እንዳረጋለን ብለዋል።
 
መድረኩ ላይ የሚቀርቡ ጥናቶች የባህላዊ ህክምና አገልግሎት፣ ግጭት አፈታት ፣ የባህልና የቋንቋ ትምህርት በሀገራችን ኢትዮጵያ የሚሉ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ያተኩራሉ።
 
አውደ ጥናቱ ነገ ይጠናቀቃል።
 
በአለባቸው አባተ
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.