Fana: At a Speed of Life!

ከ8 ቢሊየን ዶላር በላይ ኢንቨስት ለሚያደርገው ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፍ እንዲሰማራ ተፈቀደለት

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፍ ለመሰማራት የቀረበውን ጨረታ በማሸነፉ የኢትዮጵያ የኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን ፈቃድ እንዲሰጠው የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሙሉ ድምፅ አጽድቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በፌስቡክ ገፃቸው ምክር ቤቱ˝ ከፍተኛ የፈቃድ ክፍያ ዋጋ እና አስተማማኝ የሙዓለ ነዋይ ፍሰት ዕቅድ ላቀረበው ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ የኢትዮጵያ የኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን አዲስ ሀገር አቀፍ የቴሌኮም ፈቃድ እንዲሰጥ በአንድ ድምፅ  አጽድቋል˝ ብለዋል።

በዚህም በአጠቃላይ ከ8 ቢሊየን ዶላር በላይ ሙዓለ ነዋይ የሚያፈስ ሲሆን ይህም እስከ ዛሬ በኢትዮጵያ ከተደረጉት የውጪ ቀጥተኛ የሙዓለ ነዋይ ፍሰቶች ብልጫ እንዲኖረው ያደርገዋል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

ኢትዮጵያን ሙሉ ለሙሉ ወደ ዲጂታል አገልግሎት የማስገባት ዕቅዳችን ፈር ይዟል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ግልጽነት እና ውጤታማነት የሞላበት ሂደት ላሳኩ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።

ፓርትነርሺፕ ፎር ኢትዮጵያ ሳፋሪኮም ከኬንያ ፣ቮዳፎን ከብሪታኒያ ፣ቮዳኮም ከከደቡብ አፍሪካ፣ ሲዲሲ ግሩፕ ከብሪታኒያ፣ ሰሚቶሞ ኮርፖሬሽን ከጃፓን በጥምረት የያዘ የቴሌኮም ድርጅት ነው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.