Fana: At a Speed of Life!

በቢቸና ከተማ 40 ሺህ ብር ጉቦ በመቀበል የተጠረጠረው የመብራት ሀይል ስራ አሰኪያጅ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን ቢቸና ከተማ በሙስና ወንጀል የተጠረጠረው የመብራት ሀይል ስራ አሰኪያጅ በቁጥጥር ስር ውሏል።

በቢቸና ከተማ በሙስና ወንጀል የተጠረጠሩት የቢቸና የመብራት ሀይል አገልግሎት ዲስትሪክት ስራ አሰኪያጅ በቁጥጥር ስር ማዋሉን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ ነው የገለፀው።

በመምሪያው የሙስና ወንጀሎች ምርመራ ዋና ክፍል ሀላፊ የሆኑት ምክትል ኮማንደር አሸብር አምላኩ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት ስራ አሰኪያጁ ለአንድ ግለሰብ የወፍጮ ቤት ቆጣሪ አስገባልሀለሁ በማለት ከአንድ አመት በላይ ሲያጉላላው ከቆየ በኋላ 40 ሺህ ብር እጅ መንሻ እንደጠየቀው ጠቅሰው ግለሰቡም በስራ አስኪያጁ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 40 ሺህ ብሩን እንዳስገባለት በሰነድ ምርመራ ተረጋግጧል ብለዋል።

ተጠርጣሪውም ገንዘቡን ከተቀበለ በኋላ ቆጣሪውን እንዳስገባለት የግል ተበዳዩ የቃል ማስረጃ የሰጠ መሆኑን ተናግረዋል።

መምሪያው ጥቆማው ከደረሰው በኋላ ሰፊ ምርመራ ሲያደርግ መቆየቱን የተናገሩት ምክትል ኮማንደር አሸብር አሁን ላይ በቂ የሰውና የሰነድ ማስረጃ በመገኘቱ ተጠርጣሪው በህግ ቁጥጥር ስር ውሎ ተጨማሪ ምርመራ እየተደረገበት ነው ብለዋል።

በሰላም አሰፋ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.