Fana: At a Speed of Life!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከትግራይ እና ከአማራ ክልሎች ከተውጣጡ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በትግራይ ክልል የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመመለስ እና ለማቋቋም የሚያስችሉ  የትብብር መንገዶችን  በተመለከተ ከትግራይ እና ከአማራ ክልሎች ከተውጣጡ የሃይማኖት አባቶች፣ የንግዱ ማህበረሰብ አባላት እና ምሁራን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በተለይ በክልሉ የክረምቱ ወራት ከመግባቱ በፊት የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመመለስ እና ለማቋቋም ያለመ ውይይት እንደነበር ተጠቁሟል።

የፌደራል እና የክልል አመራሮችን እንዲሁም የሁለቱን ወገን ተወካዮች ጨምሮ፤ 15 ሰዎች የሚገኙበት ኮሚቴ ተዋቅሮ ሥራዎቹን የሚያሳልጥ መሆኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.