Fana: At a Speed of Life!

የናይጀሪያ ጦር አዛዥ በአውሮፕላን አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የናይጀሪያ ጦር አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ኢብራሂም አታሂሩ በአውሮፕላን አደጋ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡

የሃገሪቱ ጦር እንዳስታወቀው አዛዡን የያዘው አውሮፕላን በአስቸጋሪ የአየር ሁኔታ ለማረፍ ሲሞክር አደጋው ተከስቷል፡፡

አደጋው በሃገሪቱ ሰሜን ምዕራብ በምትገኘው የካዱና ግዛት መድረሱንም አስታውቋል፡፡

አዛዡ ባለፈው ጥር ወር ወደ ስልጣን መምጣታቸው ይታወሳል፡፡

የሃገሪቱ ፕሬዚዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ በጦር አዛዡ ህልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገልጸዋል፡፡

ምንጭ፦ ቢቢሲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.