Fana: At a Speed of Life!

ምክክሩ በአማራ እና በትግራይ ህዝብ መካከል በቀጣይ ለሚተገበሩ የሰላም ግንባታ ሂደቶች በር ከፋች ነው – ዶ/ር አብርሃም በላይ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በአማራ እና ትግራይ ክልሎች መካከል የሚካሄደውን የሰላም ግንባታ ምክክር መድረክ በሁለቱ ህዝቦች መካከል በቀጣይ ለሚተገበሩ የሰላም ግንባታ ሂደቶች በር ከፋች መሆኑን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር አብርሃም በላይ ገለጹ፡፡

ዶክተር አብርሃም፤ የምክክር መድረኩ በሁለቱ ህዝቦች መካከል ለሚተገበሩ የመግባቢያ የውይይት መድረኮችና የሰላም ግንባታ ሒደቶች ብሎም የመልሶ ማቋቋም ስራ በር ከፋች የሆነ በጎ እርምጃ መሆኑን በማህበራዊ የተስስር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡

በትግራይ ከመኖሪያ አካባቢያቸው የተፈናቀሉ ዜጎችን ከመጪው የክረምት እርሻ ወቅት መጀመር በፊት ለመመለስና በዘለቄታውም ለማቋቋም በሚቻልበት አግባብ ዙርያ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የተመራና ከፍተኛ የፌደራል መንግስት የስራ ሀላፊዎች የሁለቱ ክልል ባለሀብቶች፣ ምሁራን እና የእምነት ሰዎች በተገኙበት ምክክር መደረጉን አስታውሰዋል፡፡

በመልዕክታቸውም “መላው የአገራችን ህዝቦች ይህንን የሰላምና የህዝባዊ ግንኙነት ማበልፀጊያ ጅምር በንቃት በመከታተልና በመደገፍ ለዜጎቻችን ያላችሁን አጋርነት እንድታሳዩ በትህትና እማፀናለሁ” ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.