Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ ሲዳማ ቡና ጅማ አባ ጅፋርን አሸነፈ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 15 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲዳማ ቡና ጅማ አባ ጅፋርን 4ለ 1 አሸንፏል።

ለሲዳማ ቡና ኦኪኪ አፎላቢ በ6፣ 38 እና 71ኛው ደቂቃ ጎል በማስቆጠር ሃትሪክ ሲሰራ አራተኛውን ጎል ይገዙ ቦጋለ አስቆጥሯል።

ለጅማ አባጅፋር ብቸኛዋን ጎል በ70ኛው ደቂቃ ተመስገን ደረሰ አስቆጥሯል ።

የሲዳማ ቡናን ማሸነፍ ተከትሎ ወልቂጤ ከተማ 3ኛው ወራጅ ቡድን መሆኑን ማረጋገጡን ከሶከር ኢትዮጵያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.