Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ልማት ማህበር ኮንፈረንስ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በአራዳ ክፍለ ከተማ የኦሮሚያ ልማት ማህበር ኮንፈረንስ ተካሂዷል።

በኮንፈረንሱ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ፣የኦሮሚያ ልማት ማህበር የቦርድ ሰብሳቢ አባዱላ ገመዳ፣ የአራዳ ክፍለ ከተማ ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ሃና የሺንጉስ ፣ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ በክፍለ ከተማው የማህበሩ አባላት ተገኝተዋል።

በኮንፍረንሱ መልዕክት ያስተላለፉት ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ፤ የኦሮሚያ ልማት ማህበር ገና ከጅምሩ “አንድነት ለልማት” በሚል በጀመራቸው ስራዎች መንግስት ያልደረሰባቸውን የልማት ስራዎች በማዳረስ የበኩሉን አስተዋፅኦ እያበረከተ ይገኛል ብለዋል።

የተለያዩ ልማት ማህበራት ከህብረተሰቡ ያሰባሰቡትን ሀብት በመንግስት መሸፈን ያልቻሉ የልማት ስራዎችን በመስራት የሚያደረጉትን እንቅስቃሴ በቀጣይም አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባም ገልጸዋል።

የልማት ማህበራቱ ለሚያካሂዱት ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች የከተማ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ድጋፍና እገዛ ያደርጋል ብለዋል ምክትል ከንቲባዋ።

በቅርቡም የኦሮሚያ ልማት ማህበርን ጨምሮ የተለያዩ የልማት ማህበራት ከአዲስ አበባ የሰበሰቡትን ሀብት እዚሁ አዲስ አበባ ላይ ለማልማት ላቀረቡት እቅድ በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋና ማቅረባቸውን ከከተማው ፐረስ ሲክሬታሪ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.