Fana: At a Speed of Life!

በመንግስት ብቻ የሚሰራ ልማት ባለመኖሩ ህዝቡ ዋነኛ የልማት አቅም መሆን አለበት- አቶ ሽመልስ አብዲሳ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በመንግስት ብቻ የሚሰራ ልማት ባለመኖሩ ህዝቡ ዋነኛ የልማት አቅም በመሆን ከመንግስት ጎን መሰለፍ አለበት” ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ ተናገሩ።

በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን አመያ ወረዳ ልማት የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር በዛሬው እለት ተካሂዷል።

በፕሮግራሙ ላይ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሜጄር ጀኔራል ይልማ መርዳሳ÷ የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ሀብታሙ ተገኝና ሌሎች የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ ÷ በመንግስት ብቻ የሚሰራ ልማት ባለመኖሩ ህዝቡ ዋነኛ የልማት አቅም በመሆን ከመንግስት ጎን መሰለፍ አለበት ብለዋል።

የወረዳዋ ተወላጆችና ወዳጆች ለአመያ ልማት ከመንግስት በጀት በተጨማሪ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብሩን ለማከናወን መነሳሳታቸው የሚያስመሰግናቸው ተግባር መሆኑንም ገልጸዋል።

የክልሉ መንግስት ከዚህ በጎ ተግባር ጎን በመቆም ለወረዳው ልማት በትኩረት ይሰራል ሲሉ አረጋግጠዋል።

በአካባቢው ከፍተኛ ችግር የሆነውን የመንገድ መሰረተ ልማት ለመገንባት በመጪው መስከረም ወር ዲዛይን በመስራት ጨረታ እንደሚወጣም ጠቁመዋል።

የወረዳው ነዋሪ በአቅሙ በፈቀደው መጠን ከመንግስት ጋር ትብብሩን እንዲቀጥል ጠይቀው ÷ ትብብሩ ድህነትን ለማስወገድ ዋነኛ መንገድ መሆኑን ገልጸዋል።

አካባቢው ትርፍ አምራች በመሆኑ አርሶ አደሩ ያለውን በመቆጠብ ዘመናዊ የግብርና መሳሪያዎችን የሚያገኝበትን መንገድ ማመቻቸት እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

በገቢ ማሰባሰቢያ መርኃ ግብሩ ላይ የተገኙት የአካባቢው ተወላጅ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሜጄር ጀኔራል ይልማ መርዴሳ “ልማት የሚመጣው መንግስት፣ ባለሃብትና ህዝብ በጋራ ተቀናጅተው ሲሰሩ ነው” ብለዋል፡፡

አሁን የተጀመረው መልካም ተግባርም ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት አርአያነት ያለው ተግባር መሆኑን ጠቅሰዋል።

በገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብሩ ላይ ለልማት የሚውል 60 ሚሊየን ብር ቃል መገባቱን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.