Fana: At a Speed of Life!

ከ475 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የጎዴ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ጎዴ ከተማ ከ475 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የጎዴ የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክት ተመርቋል፡፡

የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቱን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሃመድና የኢፌዴሪ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ መርቀውታል።

ፕሮጀክቱ በግንቦት 2011 ዓ.ም የተጀመረና በሁለትአመት ጊዜ ውስጥ የተጠናቀቀ ሲሆን ÷ የግንባታ ወጪውም በአፍሪካ ልማት ባንክ፣ በፌደራል መንግሥትና በክልሉ መንግስት የተሸፈነ ነው።

ፕሮጀክቱ የዋቢ ሸበሌ ወንዝ ውሃን በማጣራት ነው ለመጠጥ ብቁ የሚያደርገው።

ፕሮጀክቱ የጎዴ ከተማ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን ለ30 አመታት ያለ ማሻሻያ ከተማን ተጠቃሚ ያደርጋልም ነው የተባለው።

የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ÷ የፌደራል መንግስት በሶማሌ ክልል በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ ገልፀው፥ ከእነዚህም በመስኖ፣ በኤሌክትሪክ፣ በግብርና፣ በውሃና በሌሎች በርካታ የልማት ሥራዎች ተሰርቷል ብለዋል።

አክለውም ዛሬ የተመረቀው የጎዴ የውሃ ፕሮጀክት የከተማዋን ነዋሪዎች የኑሮ ሁኔታን የሚቀይር ይሆናልም ነው ያሉት።

ምንም እንኳን ኢትዮጵያ ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎች ብገጥማትም በተባበረ ክንድ እንደምናልፍ አምናለሁ ፣ የህዳሴ ግድብ የሁለተኛው ዙር ሙሌትም በቅርቡ ይካሄዳል ሲሉ ተናግረዋል።

የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ በበኩላቸው÷ ይህ የጎዴ የውሃ ፕሮጀክት መጠናቀቅ በማየታቸው ደስ እንዳላቸው ገልፀዋል።

አያይዘውም የክልሉ መንግሥት ከለውጡ በኋላ በርካታ የልማት ስራ መስራቱን ጠቁመው ÷በቅርቡም ሌሎች 15 የክልሉ ከተሞች እንደዚህ አይነት የውሃ ፕሮጀክቶች ይከናወናሉ ማለታቸውን ከክልሉ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሃመድን ጨምሮ የየውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ፣ የኢፌዴሪ ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ሚኒስትር ወይዘሮ ፊልሰን አብዱላሂ፣ የሶማሌ ክልል ውሃ ቢሮ አብዱረህማን አህመድ፣የምስራቅ አፍሪካ የአፍሪካ ልማት ባንክ ዳይሬክተር ዶክተር አብዱል ካማራና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.