Fana: At a Speed of Life!

ኦቢኤን በአማራ ክልል አጣዬ ከተማና የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ለተፈናቀሉ ዜጎች 818 ኩንታል የምግብ እህል ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ /ኦቢኤን/ በአማራ ክልል አጣዬ ከተማና የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን በተከሰተው የጸጥታ ችግር ለተፈናቀሉ ዜጎች 818 ኩንታል የምግብ እህል ድጋፍ አድርጓል፡፡

ከቄያቸው ተፈናቅለው ለችግር የተጋለጡት ዜጎች ኦቢኤን ላደረገላቸው ድጋፍ አመስግነው÷ ሌሎች ተቋማትም የኦቢኤንን ፈለግ ተከትለው ተመሳሳይ ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው ጠይቀዋል፡፡

የአጣዬ ከተማ ከንቲባ አቶ አገኘው መክቴ÷ ኦቢኤን የህዝብ ወገንተኝነት ያለው የህዝብ ሚዲያ ነው ብለዋል፡፡

የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አህመድ ሀሰን በበኩላቸው÷ኦቢኤን ያደረገው ድጋፍ ለሌሎች ተቋማት ምሳሌ ሊሆን የሚችል ተግባር በመሆኑ ሌሎች ተቋማትም ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የአሮሚያ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ኦቢኤን ያደረገው አኩሪ ተግባር ታሪክ አይረሳውም ብለዋል፡፡

የቱለማ አባገዳ እና የአባገዳዎች ህብረት ጸሓፊ ጎበና ሆላ፣ ሚዲያው ህዝቦችን  ለመቀራረብ ምሳሌ የሚሆን ተግባር እየፈጸመ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የኦቢኤን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ዝናቡ አስራት በበኩላቸው ÷ሚዲያው ለብሔር ብሔረሰቦች ድምጽ ከመሆን በተጨማሪ ህዝባዊ ወገንተኝነቱን በተግባር እያሳየ ነው ብለዋል፡፡

ሚዲያዎች ህዝቦችን ለማቀራረብ እንዲሰሩም አቶ ዝናቡ ጥሪ ማቅረባቸውን ኦቢኤንን ጠቅሶ ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.