Fana: At a Speed of Life!

በቻይና  በውድድር ወቅት  በተከሰተ ከባድ የአየር ሁኔታ የ21 ሯጮች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቻይና በተካሄደ አገር አቋራጭ የተራራ (አልትራማራቶን) ውድድር ላይ በተከሰተ ከባድ የአየር ሁኔታ የ21 ሯጮች ሕይወት አልፏል።

በ100 ኪ.ሜ (60 ማይልስ) የአልትራማራ ውድድሩ በጋንሱ አውራጃ የቱሪስት ስፍራ በሆነው በቢጫ ወንዝ የድንጋይ ደን ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መካሄዱ ተገልጿል።

በወቅቱም በተከሰተው ከፍተኛ ንፋስ  እና በረዶ የቀላቀለበት ዝናብ አትሌቶቹ በመመታታቸው በውድድሩ ከተሳፉ  172 ሯጮች መካከል አንዳንዶቹ ሲጠፉ ÷21 ሯጮች ለህልፈት መዳረጋቸው ተገልጿል።

ውድድሩ ተቋርጦም  የነፍስ አድን ሥራ መጀመሩ ተመላክቷል።

በዚህም ከተሳታፊ አትሌቶች መካከል 151 የሚሆኑት ደህንነታቸው የተረጋገጠ ሲሆን÷ ከነዚህ ውስጥ ስምንቱ መቁሰላቸውም ነው ባለሥልጣናቱ የገለጹት  ፡፡

ውድድሩ ሲጀመርም  የተወሰኑ ተወዳዳሪዎችን ቁምጣ እና ቲሸርት ብቻ ለብሰው እንደነበር ነው የተገለጸው ፡፡

በሕይወት የተረፉት ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየትም ÷የአየር ሁኔታው በእይታቸው ላይ ተጽዕኞ በማሳረፉ  መንገዳቸውን መሳታቸውን ገልጸዋል።

የአየር ንብረት ትንበያው የተወሰነ ንፋስ እና ዝናብ እንደሚጠበቅ ቢተነብይም እነሱ የገጠማቸውን  ያህል የከፋ የአየር ጸባይ ሊኖር እንደሚችል አለመግለጹን  ተናግረዋል።

ሩጫው ከተጀመረ  ከሦስት ሰዓት ያህል በኋላ በተራራማው ክፍል በበረዶ ፣ በከባድ ዝናብ  በመምታቱ የአካባቢው ሙቀት መጠኑን እንዲያሽቆለቁል  ምክንያት መሆኑን በአቅራቢያው የሚገኘው የቤይን ከተማ ባለሥልጣናት ገልጸዋል ፡፡

የነፍስ አድን ስራው ሌሊቱን ሙሉ እስከ እሁድ ጠዋት የቀጠለ ሲሆን÷ ተጨማሪ የሙቀት መጠን መቀነሱ ፍለጋውን ይበልጥ ከባድ እንዳደረገው የቻይናው  የዜና አውታር ዘግቧል ፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.