Fana: At a Speed of Life!

በአጣየ እና አካባቢው የወደሙ ንብረቶች መልሶ ለመገንባት ከ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ እንደሚያስፈልግ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ኤፍራታ እና ግድም ወረዳ በአጣየ እና አካባቢው የወደሙ ንብረቶች መልሶ ለመገንባት ከ1 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ እንደሚያስፈልግ ተገለፀ።

ከዚህ ውስጥ 1 ነጥብ 1 ቢሊየን ብሩለመልሶ ግንባታ የሚያስፈልግ ሲሆን ፥ ቀሪው ደግሞ ለአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ እንደሚያስፈልግ ነው በአጣየ ከተማ እና በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን የደረሰውን ጉዳት ለማጣራትና ለመገንባት የተቋቋመው የቴክኒክ ኮሚቴ ባቀረበው ሪፖርት አስረድቷል።

የኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ አቶ ብርሃኑ ዘውዱ ከ281 በላይ ዜጎች ህይወት የጠፋ ሲሆን 197 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑንም ተናግረዋል።

በአካባቢው በደረሰው ውድመት 3 ሺህ 73 ቤቶች የወደሙ ሲሆን በአጣየ ከተማ ብቻ 1 ሺህ 529 ቤቶች ወድመዋልም ነው የተባለው።

በኤፍራታና ግድም ወደረዳ እና ኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን የደረሰውን ውድመት መልሶ ለመገንባት እና ተጎጂዎችን መልሶ ለማቋቋም ውይይት ተደርጓል።

በይስማው አደራው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.