Fana: At a Speed of Life!

ናይጄሪያ ከኮቪድ19 ህግ ጥሰት ጋር በተያያዘ 90 መንገደኞችን እያፈላለገች ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 16፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ናይጄሪያ የኮቪድ19 ህግ ጥሰዋል ያለቻቸውን 90 መንገደኞች እያፈላለገች ነው፡፡
መንገደኞቹ በቅርቡ ከብራዚል፣ ከህንድ እና ከቱርክ የመጡ መሆናቸው ታውቋል፡፡
ተፈላጊዎቹ ከፈረንጆቹ ግንቦት 8 እስከ 15 ባሉት ጊዜዎች ወደ ናይጄሪያ የገቡ ሲሆኑ ከእነዚህ ውስጥ 63ቱ ናይጄራውያን 27ቱ ደግሞ የውጭ ሃገር ዜጎች መሆናቸው ተገልጿል፡፡
መንገደኞቹ ከኮቪድ19 ጋር ተያይዞ ናይጀሪያ ያወጣቻቸውን ድንጋጌዎች ያላከበሩና የኮሮና ምርመራ ያላደረጉ መሆናቸውም ነው የተገለጸው፡፡
ተፈላጊቹ ላይም ለአንድ ዓመት የጉዞ ፓስፖርታቸውን መከልከልን ጨምሮ ማዕቀብ ሊጣልባቸው፥ እንዲሁም የውጭ ዜጎቹን ቪዛ ወይም ፈቃድ መሰረዝ እና ክስ ሊጠብቃቸው ይችላል ተብሏል፡፡
ሃገሪቱ ከኮሮና ቫይረስ ስርጭት ጋር ተያይዞ ክልከላ ከተደረገባቸው ሃገራት የሚመጡ ዜጎች እራሳቸውን ለአንድ ሳምንት አግልለው አስገዳጅ ህግ ተግብራለች፡፡
በናይጀሪያ በእንግሊዝ ሃገር ከተገኘው የቫይረሱ ዝርያ የተለየና አዲስ አይነት የኮሮና ቫይረስ ዝርያ በቅርቡ መከሰቱ ይታወሳል፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.