Fana: At a Speed of Life!

የክረምቱ ዝናብ ከደቡባዊ ቆላማ አካባቢዎች በቀር አብዛኛውን የሃገሪቷን አካባቢዎች ያዳርሳል

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በመጪው ክረምት የሚጠበቀው ዝናብ ከደቡባዊ ቆላማ አካባቢዎች በቀር አብዛኛውን የሃገሪቷን አካባቢዎች የሚያዳርስ እንደሚሆን ብሔራዊ ሚቲዮሮሎጂ ኤጀንሲ ገለጸ።

ኤጀንሲው ያለፈውን የበልግ ወቅትና መጪውን የክረምት የአየር ሁኔታ ግምገማና ትንበያ ይፋ አድርጓል።

የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር አቶ ፈጠነ ተሾመ እንዳስታወቁት ኤጀንሲው ለመጪው ክረምት የአየር ጠባይ ትንበያ ዓለም አቀፍ ሞዴሎችን በመጠቀም ትንታኔ አድርጓል።

በዚሁ መሰረት በአየር ጠባይ አዝማሚያ ትንበያው የሃገሪቱ የምዕራብ አጋማሽ አብዛኞቹ ቦታዎች ከመደበኛ በላይ ዝናብ እንደሚያገኙና በጥቂት ቦታዎችም መደበኛ ዝናብ እንደሚኖር ተናግረዋል፡፡

በክረምቱ የሚጠበቀው ዝናብ ከደቡባዊ ቆላማ አካባቢዎች በስተቀር አብዛኛውን የሃገሪቱን አካባቢዎች የሚያዳርስ እንደሚሆንም ጠቁመዋል።

በትንበያው መሰረት የሃገሪቱ ሰሜንና የሰሜን ምስራቅ አካባቢዎች በአብዛኛው መደበኛና ከመደበኛ በላይ ዝናብ ያገኛሉ ተብሎ ከሚጠበቁት አካባቢዎች ውስጥ መሆናቸውን አመልክተዋል።

እንደ ዋና ዳይሬክተሩ ገለፃ የክረምቱ የዝናብ መጠን ከሃገሪቱ ዓመታዊ የዝናብ ድርሻ ከ50 እስከ 85 በመቶ ይሸፍናል።
በመሆኑም እንደ ሃገር የተያዙ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች የተሳካ ለማድረግ ትንበያው እንደ መልካም አጋጣሚ ይወሰዳል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.