Fana: At a Speed of Life!

በጎንደር የጥምቀት በዓል ላይ በደረሰ አደጋ የ10 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 12፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በጎንደር ከተማ በተከበረው የጥምቀት በዓል በእንጨት መወጣጫ ርብራብ መደርመስ ምክንያት የ10 ሰዎች ህይወት ማለፉን የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል አስታወቀ።
 
በትናንትናው እለት በጎንደር የጥምቀት በዓልን ለመታደም ለመጡ እንግዶች የተዘጋጀው ርብራብ ተደርምሶ በበርካታ ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ይታወሳል።
 
አደጋውን አስመልክቶ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሪፈራል ሆስፒታል እንዳስታወቀው፥ በአጠቃላይ በአደጋው የተጎዱ 250 ሰዎች ወደ ሆስፒታሉ መምጣታቸውን አስታውቋል።
 
በአደጋው ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ሆስፒታል ከተወሰዱ ሰዎች መካከልም የ10 ሰዎች ህይወት ማለፉን የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር አሸናፊ ታዘበ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
 
አብዛኛዎቹ ታካሚዎች ህክምና አግኝተው ወደ ቤታቸው የተመለሱ ሲሆን፥ በሆስፒታሉ በአሁኑ ወቅት 80 ተጎጂዎች ህክምና እየተከታተሉ ይገኛሉ።
 
ከእነዚህም ውስጥ 13 ሰዎች የከፋ ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ህክምናቸው ረጅም ጊዜን የሚወስድ መሆኑንም ነው ዶክተር አሸናፊ ታዘበ ያስታወቁት።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.