Fana: At a Speed of Life!

ቦርዱ ፓርቲዎች በመራጮች መዝገብ የታዘቡትን ችግር እንዲያቀርቡ ጥሪ አቀረበ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የመራጮች መዝገብ ይፋ ማድረግን ተከትሎ በ6ኛው አጠቃላይ ምርጫ የሚወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሂደቱ የታዘቡትን እና መፈታት አለበት የሚሉትን ችግር እስከ ነገ እንዲያስገቡ ጥሪ አቀረበ፡፡

ላለፉት 10 ቀናት የተከናወነው የመራጮች መዝገብን ለህዝብ ይፋ የማድረግ ተግባር በዛሬው ዕለት ተጠናቋል፡፡

ፓርቲዎቹ ችግሩ ተከሰተበት የሚሉትን የምርጫ ክልል እና ጣቢያ በመጥቀስ አቤቱታቸውን እስከ ነገ ማታ ከቀኑ 11፡30 ድረስ እንዲያቀርቡ ቦርዱ ጠይቋል፡፡

የሚቀርቡለትን አቤቱታዎች ለመመርመር እና ለመፍታት ከፍተኛ ጥረት እንደሚያደርግ በመጥቀስም፥ የመራጮች ምዝገባ ከተጠናቀቀ በኋላ እስከ ዛሬ በነበሩት 10 ቀናት የመራጮች መዝገብ ለህዝብ ይፋ ተደርጎ ፓርቲዎች፣ ታዛቢዎች እና የሚመለከታቸው አካላት ሲመለከቱት መቆየታቸውን አስታውሷል።

የመራጮች መዝገብ ይፋ ከተደረገበት ጊዜ አንስቶ በተለያዩ ጊዜያት የመጡ አቤቱታዎችን ከፓርቲዎች በመተባበር ለመመርመር እና ለመፍታት መሞከሩንም የቦርዱ መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.