Fana: At a Speed of Life!

በአፍሪካ ሕብረት የሚካሄዳው የግድቡ ድርድር ትክክለኛ የመፍትሄ መንገድ መሆኑን ቻይና ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ላይ በአፍሪካ ሕብረት አስተባባሪነት የሚካሄደው የሦስትዮሽ ድርድር ትክክለኛ የመፍትሄ መንገድ መሆኑን በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ ምክትል የልዑክ ኃላፊ ዢ ቲያን አስታወቁ።
ዢ ቲያን በተለይ ለአዲስ ዘመን እንደገለፁት÷ ቻይና የህዳሴ ግድብን አስፈላጊነት በውል ትረዳለች ብለዋል።
በአፍሪካ ሕብረት የሚካሄደው የሦስቱ ሃገራት የሦስትዮሽ ድርድር ለመፍትሄው ትክክለኛ መንገድ ነው፣ ለድርድር ሂደቱም አስፈላጊውን ድጋፍ ታደርጋለች ነው ያሉት።
የህዳሴ ግድቡ የዓለም አቀፉን ኅብረተሰብ ቀልብ እየሳበ መሆኑን ያስታወሱት ዢ ቲያን÷ እንደ አንድ የአፍሪካ ወዳጅ ሃገር ቻይና የግድቡ አስፈላጊነት በተለይም ለኢትዮጵያ ልማት ያለውን ጠቃሜታ በውል ስለምትረዳ በአፍሪካ ህብረት አስተባባሪነት የሚካሄደውን ድርድር እንደምታበረታታ አስታውቀዋል።
አካሄዱ መፍትሄ ለማግኘት ትክክለኛ መንገድ መሆኑን ጠቁመው÷ ̎እኛ ለአፍሪካዊ ችግሮችና ጉዳዮች አፍሪካዊ መፍትሄዎች እንዲያገኙ እንደግፋለን˝ ብለዋል።
እያንዳንዱ ሃገርም ድርድሩን በሰላማዊ መንገድ በመቀጠል በሦስቱ ወገኖች በኩል ተቀባይነት ያለው መፍትሄ እንዲያገኙ እናበረታታለን ሲሉ ገልጸዋል።
ከሦስቱም ተደራዳሪ ሃገራት ጋር የጠበቀ ግንኙነት ስላለን ሁሉም አካላት ድርድሩን በሰላማዊ መንገድ እንዲቀጥሉና ስምምነት ላይ እንዲደርሱ እገዛ እናደርጋለንም ነው ያሉት።
ቻይና በአፍሪካ ህብረት አዳራደሪነት ያለማንም ጣልቃ ገብነት ለሚካሄደውን የሦስቱ ሃገራት ድርድር ዘላቂ መፍትሄ እንዲያመጣ ሀገራቸው ድጋፍ እንደምታደርግም አስገንዝበዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.