Fana: At a Speed of Life!

የሰላም ዋነኛው ምሰሶ የህብረተሰቡ  በጎነት በመሆኑ ሁሉም ሠላምን ለማስጠበቅ በጋራ መስራት ይገባዋል- አቶ ገዱ አንዳርጋቸው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)  የሰላም ዋነኛው ምሰሶ የህብረተሰቡ  በጎነት በመሆኑ ሁሉም ሠላምን ለማስጠበቅ በጋራ መስራት ይገባዋል ሲሉ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ገለጹ።

ይህ የተባለው የወሎ ዩኒቨርስቲ  የመቅደላ አምባ ዩኒቨርስቲና የደቡብ ወሎ ዞን በጋራ ባዘጋጁት” ሰላም ለሁሉም፤ሁሉም ለሰላም ”  በተሰኘ የሰላም የውይይት መድረክ  ላይ ነው።

በውይይቱ ላይ የተገኙት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው÷ በወሎ አካባቢ የሚታየውን የሰላም እሴት በማጠናከር ሀገራዊ ሰላምን ለማረጋገጥ ሁሉም በጋራ ሊሰራ ይገባል ብለዋል።

ከግጭት ትርፍ የለም ያሉት አቶ ገዱ ሰላምን በሁሉም የሀገሪቱ ጫፍ ለማረጋገጥ ማህበረሰቡ ዋናው ምሰሶ በመሆኑ ከመንግስት ጋር ስለ ሰላም  በጋራ መስራት አለበትም ነው ያሉት።

የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ሰይድ መሀመድ በበኩላቸው÷ የሀይማኖት  አባቶች የሀገር ሽማግሌዎች የጸጥታ ሀይሎች እንዲሁም ማህበረሰቡ ሀገርን ለማሻገር እያደረጉ ያሉትን ጥረት አጠናክረው መቀጠል አለባቸው  ብለዋል።

በውይይቱ ላይ የአማራ ክልል የህዝብ ሠላምና ደህንነት ቢሮ ሀላፌ ዶክተር ሰማ ጥሩነህን ጨምሮ የክልልና የዞን አመራሮች የሀይማኖት አባቶችና የሀገር ሽማግሌዎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

በከድር መሀመድ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.