Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያ ከአፍሪካ ጋር ላላት ግንኙነት ዋጋ እንደምትሰጥና ድጋፏን እንደምትቀጥል ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ ከአፍሪካ ጋር ላላት ግንኙነት ዋጋ እንደምትሰጥ እና ድጋፏን እንደምትቀጥል የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ገለጹ።
ፕሬዚዳንቱ ለአፍሪካ ቀን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በመልዕክታቸው አፍሪካውያን በቅኝ ግዛት ላይ የተቀዳጁት ድል ለነጻነት፣ ሰላም እና ብልጽግና ያላቸውን ፍላጎት ያሳየ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
በዚህም አፍሪካውያን በማህበራዊ እና ኢኮኖሚያው ዘርፎች አስደናቂ ስኬቶችን አስመዝግበዋል ነው ያሉት፡፡
ከዚህ ባለፈም አፍሪካውያን በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ እየተጫወቱ ያሉት ሚና እያደገ መምጣቱንም ፕሬዚዳንቱ የገለጹት፡፡
በተለያዩ ዘርፎች የተጀመሩትን የሩሲያ-አፍሪካ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናር እንደሚቻል በማንሳትም፥ ሀገራቸው ለዚህ ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል፡፡
የአፍሪካ ህብረት እና ሌሎች ቀጠናዊ ትብብሮችን በማሳደግ እንዲሁም የጋራ ተጠቃሚነትን እና ቅንጅትን በመፍጠር እንደሚጠቅምም አንስተዋል፡፡
ሩሲያ ከአፍሪካ ጋር ላላት ግንኙነት ዋጋ ትሰጠዋለች ፣ የማይናወጥ ድጋፋችንን በመቀጠል አካባቢያዊ ግጭቶችን በመፍታት፣ ሽብርተኝነትን በመከላከል፣ ጽንፈኝነትን እና ተላላፊ በሽታዎችን በመከላከል፣ በአህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ እንሰራለን ማለታቸውን በኢትዮጵያ ከሩሲያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.