Fana: At a Speed of Life!

ለትምህርት ቤቶች “ኮቪድ-19 ኢትዮጵያ” የተሰኘ መተግበሪያ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለትምህርት ቤት አስተዳደር ሠራተኞች እና ለመምህራን የኮሮና ቫይረስ ሥርጭትን መከላከል እና ለቁጥጥር ሥራ የግንዛቤ ማስጨበጫ ለመስጠት “ኮቪድ-19 ኢትዮጵያ” መተግበሪያ ይፋ ሆነ።
የግንዛቤ ማስጨበጫ መተግበሪያው ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ማካተቱ ተገልጿል።
የኮሮና ቫይረስ መተግበሪያው በጤና እና ትምህርት ሚኒስቴር በጋራ የተዘጋጀውን የኮሮና ቫይረስ መከላከል መመሪያን መሠረት ያደረገ ነውም ተብሏል፡፡
መተግበሪያው የበሽታ ቅኝት፣ የተግባቦት እና የማኅበረሰብ ተሳትፎ ሥራዎችን እንዲሁም በሁሉም ደረጃ ስላለው ኃላፊነቶች የግንዛቤ ማስጨበጫ እንደሚሰጥ ተገልጿል።
በመጨረሻም “ኮቪድ-19 ኢትዮጵያ” መተግበሪያን ሁሉም መምህራን እና የትምህርት ቤት አስተዳደር ሠራተኞች በስልካቸው በመጫን ስልጠናውን እንዲወስዱ እና ለኮሮና ቫይረስ ሥርጭት ቁጥጥር ሥራ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ጥሪ መቅረቡን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.